በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ አካባቢ የሚኖሩት ሕፃናት ትምህርት በገንዘብ እጥረት ሳቢያ አደጋ አንዣቦበታል አለ፡፡
አዲስ አበባ —
በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ አካባቢ የሚኖሩት ሕፃናት ትምህርት በገንዘብ እጥረት ሳቢያ አደጋ አንዣቦበታል አለ፡፡
ከሚፈለገው ገንዘብ አሥራ ሁለት በመቶውን ብቻ እንዳገኘም አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያም ከሁለት መቶ በላይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ መግለጫው ጠቁሟል፡፡
የዩኒሴፍ መግለጫ እንደሚለው ግጭቶች እና በአደጋ ምክንያት ውድመት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት ትምህርት በገንዘብ እጥረት ምክንያት ለአደጋ ክፉኛ ተጋልጧል፡፡ ለእነዚህ ሕፃናት ትምህርት ከሚፈለገው 9መቶ 32 ሚሊዮን ዶላር ዩኒሴፍ በእጁ የገባው 1መቶ 15 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነም ዓለምቀፉ ድርጅት ያወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5