ኮሌራ በአስር የአፍሪካ ሀገሮች መዛመቱ ተመድን አሳስቧል

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ኮሌራ በአስር የአፍሪካ ሀገሮች መዛመቱ ተመ ድን አሳስቧል

የኮሌራ ወረርሽኝ ቢያንስ በአስር የአፍሪካ ሀገሮች ተዛምቷል፡፡ ይህም የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍን ያሳሰበ ሲሆን በተለይ የዛምቢያ እና የዚምባቡዌ የወረርሺኙ ይዞታ በጣም አስጊ መሆኑን ዩኒሴፍ አመልክቷል፡፡ እንደ የዓለም የጤና ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ድጋፍ ለማግኘት ይቻል ዘንድ የዚምባቡዌ መንግሥት ውሃ ወለዱን በሽታ ብሄራዊ አደጋ ብሎ እንዲያውጅ የሀገሪቱ የጤና አዋቂዎች በማሳሰብ ላይ ናቸው፡፡

ኮለምበስ ማቩንጋ ከሐራሬ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።