በጦርነት ከታመሰችው ደቡብ ሱዳን ወደአጎራባች ዩጋንዳ የተሰደዱት ዜጎቿ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መብለጡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
የመንግሥታቱ ድርጅት የሥደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ በየዕለቱ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ደቡብ ሱዳናውያን ዩጋንዳ መግባታቸውን ገልፀዋል። ሊሎች አንድ ሚሊዮን ደግሞ ወደኢትዮጲያ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ መሰደዳቸውን ጨምሮ ገልፀዋል።