ትሪፖሊ ውስጥ ግጭት በመበባሱና የፀጥታ ሁኔታው እየከፋ በመሄዱ 149 የሚሆኑ ለአደጋ የተጋለጡ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሮም ተወስደዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ወደ ሮም የተወሰዱት ሰዎች ኤርትራውያን፣ ኢትዮጵያውያን፣ ሶላሌዎችና ሱዳናውያን ይገኙባቸዋል ተብሏል። 65 ልጆች፣ 13ቱ ከአንድ ዓመት ዕድሜ በታች የሆናቸው ህፃናት ናቸው።
አብዛኞቹ በምግብ ዕጥረት የሚሰቃዩ ሲሆኑ ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው ታውቋል።
ሰዎቹ በተለያዩ እስር ቤቶች በአስከፊ ሁኔታ ሲሰቃዩ ከቆዩ በኋላ፣ በሊብያና በጣልያን ባለሥልጣኖች ትብብር እንደተወሰዱ ተዘግቧል።