አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላም ሚኒስቴር አማካኝነት በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ ሁኔታ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማብራሪያ መስጠቱ ተገለፀ። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚል፤ መሥሪያ ቤታቸው በኢትዮጵያ ለሚገኙት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ ፊልፖ ግራንዲ የተሰጠውን ማብራሪያ በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት አጠር ያለ ገለፃ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ሕግን ለማስከበር ከወሰደው እርምጃ በኋላ በሰብዓዊ ሁኔታው ዙሪያ እየተከናወኑ ነው ያሉትን ሥራ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊዎች አስረድተዋል።
በተለይም በኢትዮጵያ በአራት የስደተኛ ማቆያ መጠለያ ውስጥ ስለሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኖች ማብራሪያ ተሰጥቷል ብለዋል። ኮሚሽነሩም የተሠሩ ሥራዎችን በአካል ተገኝተው እንደሚመለከቱ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5