Your browser doesn’t support HTML5
ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ በቀረው እና ከመቼውም በላይ ወሳኝ መሆኑ በሚነገርለት የዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሂደት ቁልፍ የሆነ ጉዳይ ነው የተከታዩ ውይይት ትኩረት።
በእንግሊዝኛው አጠራሩ ‘ኢሌክቶራል ኮሌጅ’ ይባላል።
ዘመን የጠገበው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ስርዓት አንድ አካል ቢሆንም፣ በብዙዎች ዘንድ በስፋት እና በወጉ አይታወቅም።
በዩናይትድ ስቴትስ ህገመንግሥት መሰረት አንድ ዕጩ አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ከሰጡት አጠቃላይ ድምጽ የአብላጫውን ድምጽ በማግኘቱ ብቻ (በዚህ ‘ኢሌክቶራል ኮሌጅ’ በተባለ የምርጫ ሥርዓት በሚያገኘውም የድምጽ ቆጠራ አሸናፊ ካልሆነ በስተቀር) ቀጣዩ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ አይበቃም።
ለመሆኑ ‘ኢሌክቶራል ኮሌጅ’ ምንድነው? የምርጫውን ውጤት የሚወስነውስ እንዴት ይሆን? ምላሹን ከተያያዘው የድምጽ ማጫወቻ ያገኛሉ።
ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን ዶ/ር ፋሲል ቸርነት የጆርጂያ ስቴት ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስ ትምሕርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው።