‘ናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር’ - ከበሽታ የሚፈረጅ እጅግ የበዛ ራስ ወዳድነት እና ጣጣው

Your browser doesn’t support HTML5

‘ናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር’ - ከበሽታ የሚፈረጅ እጅግ የበዛ ራስ ወዳድነት እና ጣጣው

በአንድ በኩል ስለ ራስ የሚኖር ከልክ ያለፈ የታላቅነት ስሜት እና ከልክ ያለፈ አድናቆት የመሻት አባዜ፤ በሌላው በኩል ደግሞ በሌሎች ሰዎች ላይ ተረማምዶ ራስን የማበልጸግ ፍላጎት እና ለሌሎች ስቃይ ደንታ ቢስ በመሆን ከጉዳታቸው ለማትረፍ መወጠን የ‘ናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር’ ዋና ዋና መለያዎች መሆናቸውን ባለሞያዎች ያስረዳሉ።

‘ናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር’ በሚል በእንግሊዝኛ መጠሪያው ይበልጥ የሚታወቀውን ይህን የአእምሮ ጤና ሁከት፡ ሰዎች ገነን ብሎ ከሚታይ ለራስ ያደረ ፍቅር የሚንጸባረቅበት የአንዳንዶች ጠባይ ጋር ያመሳስሉት እንጂ ሕክምና የሚሻ እና በተገቢው ሃኪም ምርመራ መለየት እንዳለበት እንግዳችን ያስረዳሉ።

ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን ዶ/ር ተሾመ ሽብሬ የአእምሮ ሃኪም እና በካናዳዎቹ የዴል ሃውሲ እና የሜሞሪያል ዩኒቨርሲቲዎች ረዳት የሕክምና ፕሮፌሰር ናቸው።

ሙሉ ቅንብሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ።