‘ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ’ እና በአእምሮ ጤና ላይ ያለው አንድምታ

Your browser doesn’t support HTML5

‘ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ’ እና በአእምሮ ጤና ላይ ያለው አንድምታ

ስሜትን ጠንቅቆ የማወቅ፣ የመግራት እና በአግባቡ የመግለጽ፤ የሌሎችንም በቅጡ የመረዳት በወጉ የማስናገድ ክህሎት፣ ‘ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ’ በሚለው የእንግሊዝኛ መጠሪያው ይታወቃል። ይህን ክህሎት ማዳበር ከሰዎች ጋራ በሚኖረን ተግባቦት፣ በሥራ ቦታ እና በቤተሰባዊ ሕይወት፤ ብሎም በሌሎች ማኅበራዊ ግንኙነቶቻች ጭምር ለስኬት እንድንበቃ የሚያግዝ መኾኑ በባለሞያዎች ይታመናል።

በግል ህይወትም ይሁን በተሰማሩበት የሞያ መስክ ካለሙበት ለመድረስ ቁልፍ ተደርጎ የሚታየው ይህ ክህሎት፣ እንደ ጭንቀት እና ድባቴ የመሳሰሉትን ጨምሮ ለአንዳንድ የአዕምሮ ጤና ሁከቶች የመጋለጥ እጣን በእጅጉ መቀነስ እንዳስቻለም ተገልጿል።

የክህሎቱን ፋይዳ እና ይልቁንም በአእምሮ ጤና ላይ ያለውን አንድምታ በሚዳስሰው በዚህ ቅንብር ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን የነርቭ እና የሕክምና ስነ ልቦና ባለ ሞያው ዶ/ር ሳሙኤል ወልዴ ናቸው።

ዶ/ር ሳሙኤል በግራንድ ኬንየን ዩኒቨርሲቲ የሕክምና መምሕር እና ደራሲም ናቸው።