ማርቲን ግሪፊትስ የኢትዮጵያ ተልኳቸውን ዛሬ ጀምረዋል

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፊትስ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፊትስ የኢትዮጵያ ተልኳቸውን ዛሬ ጀምረዋል፡፡

ግሪፊትስ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

ረዳት ዋና ጸሐፊው በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ ሁኔታና የረድኤት ድርጅቶቹ ተረጅዎቹ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ለመድረስ ስለገጠማቸው ፈተናዎች ገንቢ የሆነ ውይይት ማድረጋቸውም ተመልክቷል፡፡

በነገው ዕለትም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከተባበሩት መንግሥታት ወኪሎችና የዲምፕሎማሲው ማኅበረሰብ ጋር የሰብዓዊ ዕርዳታ ስለሚፈልጉ በሚሊዮን ስለሚቆጠሩ ተረጅዎችን ለመርዳት ስለሚደረገ ጥረት ለመነጋገር ማቀዳቸው ተገልጧል፡፡

ግጭት ድርቅ የጎርፍ አደጋ የበሽታ ወረርሽኝ እና የበረሃ አምበጣ መኖራቸው በመላው ኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ በቀጣይነት አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

20 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች እርዳታ እንዲሰጣቸው የታሰበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 7 ሚሊዮን የሚሆኑን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት በቀጥታ ተጠቂ መሆናቸው በመግለጫው ተገልጿል፡፡

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የሰብዓዊ እርዳታ ምላሽ ከሚያስፈልገው ውስጥ የ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ክፍተት እንዳለ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ወደ 606 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገው እርዳታን ለማንቀሳቀስ የዋለ ሲሆን 474 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ደግሞ ከትግራይ ውጭ ለሆኑ አካባቢዎች የሰብዓዊ እርዳታው ተደራሽነት ለተነደፈው እቅድ የዋለ መሆኑም ተገለጿል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ እየጨመረ የመጣውን የእርዳታ ፍላጎት የሚያሟላ አይደለም፡፡ ያለው የድርጅቱ መግለጫ

ከኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጄንሲና የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ወደ 700ሺ ለሚጠጉ ስደተኞች የሚሰጠው የምግብ እርዳታ እንዳይቋረጥ በጋራ ባቀረቡት ተማጽኖ 68 ሚሊዮን ዶላር መጠየቃቸውን ጠሷል፡፡