የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጦርነት በተበጠበጠችው የመን ውስጥ ለሚኖሩ 12 ሚሊዮን ሕዝብ ነፍስ አድን የሚሆን የ2.1 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ጠየቀ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም የሳውዲ አረቢያ ጣምራ ኃይል ሀገሪቱን በቦምብ መደበደብ ከጀመረ ወዲህ የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛ የእርዳታ ተማጽኖ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው ነው።
ድርጅቱ ዛሬ ተማጽኖውን ካሰማበት ጄኔቫ ከተማ ዘጋቢያችን ሊሳሽ ላይን ተከታዩን ልካለች።
ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።
Your browser doesn’t support HTML5