ተመድ ስለሮሒንግያ ሙስሊሞች

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

የማያንማር ወታደራዊ ሃይል ባለፈው አመት የሮሒንግያ ሙስሊሞች ላይ በርካታ የጭካኔ ተግባሮች ፈጽሟል የሚለው ልዩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቡድን ስላገኘው መረጃ ለድርጅቱ የፀጥታ ምክር ቤት ያቀርባል።

የማያንማር ወታደራዊ ሃይል ባለፈው አመት የሮሒንግያ ሙስሊሞች ላይ በርካታ የጭካኔ ተግባሮች ፈጽሟል የሚለው ልዩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቡድን ስላገኘው መረጃ ለድርጅቱ የፀጥታ ምክር ቤት ያቀርባል።

ከ15ቱ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ዘጠኙ፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ አይቮሪኮስት፣ ኒዘርላንድስ፣ ፔሩ፣ ፖላንድ፣ ስዊድንና ዩናይትድ ስቴትስ በያዝነው ወር ከልዩው ቡድን መሪ ጋር ተገናኝተው መነጋገር እንደሚፈልጉ ትላንት ጥያቄ አቅርበዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የማያንማር አምባሳደር ሀዩ ዱ ሱን በበኩላቸው በላኩት ደብዳቤ ስብሰባ መጠራቱን ተቃውመዋል። ለተደረጉት ሌሎች መሻሻሎች ዕውቅና ሳይሰጡ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚጠይቁ ከሆነ “መጨረሻው ውድቀት የሚሆን አደገኛ ጥረት ነው” በማለት አስጠንቅቀዋል።