የሰሜን ኮሪያ የኒክሊየር ሙከራ፣ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አዲስ የኢኮኖሚ ማዕቀብ

  • ቪኦኤ ዜና
በቅርቡ ሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለውን ዓለማቀፍ ማዕቀብ፣ የእስያ ሀገሮች በአዎንታዊ መልኩ ዕያዩት ሲሆን፣ ብዙዎቹ ግን፣ ተጨባጭ ውጤት ስለማስገኘቱ፣ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተገለፀ።

በቅርቡ ሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለውን ዓለማቀፍ ማዕቀብ፣ የእስያ ሀገሮች በአዎንታዊ መልኩ ዕያዩት ሲሆን፣ ብዙዎቹ ግን፣ ተጨባጭ ውጤት ስለማስገኘቱ፣ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተገለፀ።

ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ሳምንት ባካሄደችው፣ ምናልባትን ሃይድሮጂን ቦምብ ሊሆን እንደሚችል በተገመተው የኑክሊየር ሙከራ፣ የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት ሰኞ፣ አዲስና ጠንከር ያለ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንደጣለባት ታውቋል።

“ዛሬ ዓለም፣ በምንም ዓይነት የኑክሊየር ቦምብ ባለቤት የሆነችውን ሰሜን ኮሪያን ሊቀበል አይችልም” ሲሉ ትናንት ሰኞ ለፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የገለፁት፣ በተመድ የዩናይትድ ስቴትሷ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ ናቸው።