ተመድ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

ኢትዮጵያ ውስጥ ሁከት መበርታቱና የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መታወጁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊን እጅግ አብዝቶ እንደሚያሳስባቸው ቃል አቀባያቸው አስታወቁ።

የኢትዮጵያ አለመረጋጋግትና ስፋት ያለው አካባቢዋ ጉዳይም አሳሳቢ መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

በፀብ መፈላለጉ ፈጥኖ እንዲቆም፤ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ህይወት አድን ድጋፍ ባልተገደበ ሁኔታ መድረስ እንዲችል፤ ለቀውሱ መፍትኄ ለማግኘትና በመላ ሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የሚያስችል መሠረት ለመጣል አቃፊ ብሄራዊ ንግግር እንዲካሄድ ዋና ፀሃፊው እንደሚጠይቁ ቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱያሪች አመልክተዋል።