የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እየሩሳሌምን በእሥራኤል ዋና ከተማነት ዕውቅና መስጠታቸውን ውድቅ የሚያደርገው ረቂቅ ውሣኔ ላይ ዛሬ ድምፅ ይሰጣል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እየሩሳሌምን በእሥራኤል ዋና ከተማነት ዕውቅና መስጠታቸውን ውድቅ የሚያደርገው ረቂቅ ውሣኔ ላይ ዛሬ ድምፅ ይሰጣል።
ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅን የመሻር መብት ካላቸው የምክር ቤቱ አባላት አንዷ በመሆነዋ ግብፅ ያቀረበችው ረቂቅ ውሣኔ የማለፍ ዕድል የሚኖረው አይመስልም።
ግብፅ ለምክር ቤቱ ያቀረበችው ረቂቅ ውሳኔ ሚስተር ትረምፕ እየሩሳሌምን በእሥራኤል ዋና ከተማነት ማወቃቸው እና የዩናይትድ ስቴትስን ኢምባሲ ከቴላቪቭ ወደእየሩስሌም የማዛወር ሂደት ሊጀምሩ መወሰናቸው በጥልቅ የሚያሳዝን ነው ሲል ያስነብባል።