የተመድ ሪፖርት

  • ቪኦኤ ዜና
የአየር ንብረት ለውጥ፣ ግጭጥና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ከ113 ሚልዮን በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ የምግብ እጥረት ማስከታላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት የምግብ ቀውስን አስመልክቶ ያወጣው ዓመታዊ ዘገባ የምግብ እጥረት ከገጠማቸው 53 ሀገሮች አስቸኳይ የምግብ ረድዔት የሚያስፈልጋት የመን መሆኗን ከዚያም የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክና አፍጋኒስታን መሆናቸውን ጠቁሟል።

የምግብና የእርሻ ድርጅት ዘገባ እንደሚለው የምግብ እጥረት የገጠማቸው ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ሚልዮን ሲደርስ ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመታት ነው። በርግጥ ከሁለት ዓመታት በፊት ከነበረው 124 ሚልዮን የተሻለ መሆኑን ተገልጿል፡፡ አንዳንድ ሃገሮችም በድርቅና በጎርፍ እንዳልተጎዱ ጥናቱ አመልክቷል።