ተመድ የኤርትራ መንግሥት ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅን እንዲፈታ ጠየቀ

  • ቆንጂት ታየ

ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ

የኤርትራ መንግሥት የታላቁ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ተሸላሚ የሆነውንና ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ መልቀቅ አለበት ሲሉ አንድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኤክስፐርት አሳሰቡ።

የኤርትራ መንግሥት የታላቁ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ተሸላሚ የሆነውንና ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ መልቀቅ አለበት ሲሉ አንድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኤክስፐርት አሳሰቡ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ኤርትራ ሰብዓዊ መብት ይዞታ ልዩ መርማሪ ሺላ ኪታሩት የዘንድሮ የ2017 የዓለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ለታሳሪው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ መሰጠቱን ምክንያት በማድረግ ባወጡት መግለጫ የአስመራ ባለሥልጣናት ሌሎቹንም በሕገወጥ መንገድ ያሰሩዋቸውን በሙሉ እንዲለቁ ጠይቀዋል።

ለጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ የተሰጠውን የዩኔስኮና የጉሌይረሞ ካኖ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማት እና ሃያ አምስት ሺሕ ዶላር የጋዜጠኛው ልጅ ቤተልሄም ዳዊት ተገኝታ ተቀብላለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ተመድ የኤርትራ መንግሥት ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅን እንዲፈታ ጠየቀ