ዋሺንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት “ያልተፈቀደ ቃለ ምልልስ” ያለውን በመጥቀስ ለትግራይ አማጽያን በሚያደሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ገሸሽ ተደርገናል ያሉትን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ ለጊዜው ሥራቸውን እንዲያቆሙ አደረገ።
ትናንት ሰኞ በተፃፈ እና ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እጅ በገባ ደብዳቤ ነው የድርጅቱ የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ኃላፊ ማውሪን አቺንግ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የተረጋገጠው።
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳዬ “ጣልቃ ገብተዋል” በሚል ባለፈው ወር ሌሎች ሰባት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ከሃገር ለማባረር በወሰደችው እርምጃ ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ ገና አልተመለሰም የተባለውን የእርዳታ አቅርቦት ሥራ ይበልጥ እንዳያዳክመው ሥጋት አሳድሯል።
ዜናው የተሰማው በሰሜን ኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለው እና ከ11 ወራት በላይ ያስቆጠረው ጦርነት እንደ መንግስታቱ ድርጅትም ግምት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለቸነፈር ወደሚያጋልጥ አዝማሚያ እያመራና እያየለ የመጣ ዓለም አቀፍ በቀሰቀሰበት የተወሳሰበ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን የኤኤፍፒ ዘገባ አትቷል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5