የተመድ የመን ጠረፍ ላይ የቆመውን የነዳጅ ጫኝ መርከብ ለማንቀሳቀስ 33 ሚሊዮን ዶላር አሰባሰበ

ፎቶ ፋይል፦ የሳተላይት ምስሉ የሚያሳየው ነዳጅ ጫኝ መርከቧን ነው፣ የመን እአአ ሰኔ 17/ 2020

ከየመን የባህር ጠረፍ ላይ ቆሞ እየዛገ ላይ ያለውን ሙሉውን ነዳጅ የጫነ መርከብ ለማስነሳት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠላሳ ሦስት ሚሊዮን ዶላር መዋጮ አሰባስቧል፡፡ ሆኖም የተሰበሰበው ገንዘብ ከሚያስፈልገው እጅግ በጣም ያነሰ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

መርከቡ እዝያው በቆመበት ከጥቅም ውጪ ከሆነ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ መጠነ ሰፊ አደጋ ሊያስከትል አንደሚችል ተገልጿል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የ144 ሚሊዮን ዶላር መዋጮ ጠይቆ የነበረ ሲሆን ከዚያ ውስጥ ሰማኒያ ሚሊዮኑ መርከቡ ላይ ያለውን ከአንድ ሚሊዮን በርሜል የሚበልጥ ነዳጅ ወደሌላ ማከማቻ ለማዛወር የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡