የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለምቀፍ ፍርድ ቤት ሚያንማር በሮሒንግያ ሙስሊሞች ላይ ማንኛውንም ዓይነት የፍጅት ተግባር እንዳይፈጸም ለመከላከል እንድትጥር ትእዛዝ ሰጥቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የሚያንማር ወታደርዊ ኃይል ከሁለት ዓመታት በፊት በሮሒንግያዎች ላይ በወሰደው የማጥቃት ዕርምጃ ምክንያት ከመኖርያቸው ለመፈናቀ እንደተገደዱ ተገልጿል።
ዓለምቀፉ ፍ/ቤት ዛሬ ይህን ትዕዛዝ የሰጠው 57 አባል ሀገሮችን ያቀፈውን እስላማዊ ትብብር የሚባለውን ድርጅት ወክላ የምዕራብ አፍሪካይቱ ሃገር ናሚብያ በሚያንማር ላይ ያቀረበችውን ክስ መሰረት በማድረግ ነው።