የኤርትራን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ የሚከታተሉት የተመድ ልዩ መርማሪ ስለኤርትራ

  • ቪኦኤ ዜና
ኤርትራ ውስጥ በቅርቡ የተወሰዱትን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴዎችን የመገደብ ዕርምጃዎች የኦርቶዶክስ እና የሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት አባላት በዘፈቀደ መታሰራቸው እጅጉን ያሳሰባቸው መሆኑን የኤርትራን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ የሚከታተሉት የተመድ ልዩ መርማሪ አስታወቁ።

ልዩ ራፖርተሯ ዳንዬላ ክራቬትስ የክልሉ የሰላምና የመረጋጋት ድባባ ቢሻሻልም እነዚህ አድራጎቶች የሚያሳዩት ሀገሪቱ ውስጥ ያለው የሰብዓዊ መብት አለመለወጡን ነው ብለዋል።

አክለውም ኤርትራ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነቷ ያሉባትን ዓለም አቀፍ ግዴታዎች በማክበር የሃይማኖት ተቁዋማት በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ እንድትፈቅድ የመላ ህዝቡን መብቶችና ሃይማኖቶች እንድታከብር አሳስባለሁ ብለዋል።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሚካሄዱ የጤና ማዕከሎች ባለፈው ሳምንት በኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናት ትዕዛዝ መወረሳቸውን የገለጠው የተመዷ ልዩ መርማሪ መግለጫ አንዳንድ የጤና ማዕከሎች በወታደር ሲጠበቁ እና ታካሚዎች ውጡ ተብለው እንደታዘዙ እና ሰራተኞችን እንዳስፈሯሯቸው መረጃ ደርሶናል ብሉዋል።

የጤን ማዕከላቱ መወረስ በተለይ አገልግሎቱን ሳያገኝ የቆየውን የገጠሩን ነዋሪ የሚጎዳ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡