በአየር ንብረት ብክለት ጉዳይ በተመድ ችሎት ሙግት ተከፍቷል

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በአየር ንብረት ብክለት ጉዳይ በተመድ ችሎት ሙግት ተከፍቷል

የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ወሳኝ ነው የተባለ የሕግ ሙግት ሄግ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት ቀርቧል። ሙግቱ ሃገራት የአየር ንብረትን ለመጠበቅ ያለባቸውን ግዴታና ጉዳት ካደረሱም የሚከፍሉትን ካሳ በተመለከተ ግልጽ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

በርካታ ትናንሽ የደሴት ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክን ያት ህልውናቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ ይከራከራሉ።

ሄንሪ ሪጅዌል ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።