የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሶሪያ የታወጀው ለአንድ ወር የሚዘልቅ ተኩስ አቁም ተግባራዊ እንዲሆን መወትወቱን አላቆመም፣ አያቆምምም ሲሉ የድርጅቱ የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ ስቴፋን ደ ሚስቱራ ተናገሩ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —

የመንግሥቱ ደጋፊ ኃይሎችና ተቃዋሚ ኃይሎች መታኮሳቸው አቁመው ርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ለሲቪሉ ህዝብ እንዲደርሱለት ዕድል እንዲሰጡ ደ ሚስቱራ ዛሬ ጄኔቫ ውስጥ ባደረጉት ንግግር ጠይቀዋል፡፡