ሩሲያ በጥቁር ባህር ዳርቻ ያሉ አካባቢዎችን በሚሳይል መደብደቧን ዩክሬን ተናግረች

በኦዴሳ ክልል፣ ዩክሬን ውስጥ የገብስ ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት

በኦዴሳ ክልል፣ ዩክሬን ውስጥ የገብስ ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት

ዩክሬን ሩሲያ በጥቁሩ ባህር ዳርቻ ያሉ ይዞታዎቼን ዛሬ ማክሰኞ በሚሳይል አጥታለች ስትል አስታወቀች።

ከጥቂት ቀናት በፊትም ሩሲያ በዩክሬን ኦዴሳ ወደብ ላይ የሚሳይል ጥቃት ያደረሰች ሲሆን ድርጊቱ ዩክሬን የእህል አቅርቦት ወደውጭ መላክ እንድትቀጥል በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተደረሰውን ሥምምነት ተግባራዊነት ጥያቄ ማጫሩ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሰኞ የተመድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከዩክሬን የዕህል አቅርቦት መውጣት ይጀምራል ሲል አስታውቋል።

ኪየቭ ኢንዲፔንዴንት የተባለ ነፃ የዜና አውታር እንደዘገበው የዩክሬን የመሰረተ ልማት ሚኒስትር እህል ወደውጭ የመላክ እንቅስቃሴው ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ይቀጥላል ብለዋል።