እንግሊዝ ፍልሰተኞችን የማስወጣት ሥራዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

ፎቶ ፋይል- ፍልሰተኞች በትናንሽ ጀልባዎች የእንግሊዝን ቻናል እያቋረጡ

ፎቶ ፋይል- ፍልሰተኞች በትናንሽ ጀልባዎች የእንግሊዝን ቻናል እያቋረጡ

የእንግሊዝ መንግስት ‘መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች’ የሚላቸውን ከሃገር የማስወጣቱን ሥራ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር ዛሬ አስታውቋል።

የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የግል ኮንትራችተሮች ፍልሰተኞቹን ወደ መጡበት ሃገር በመመለስ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ማስታወቂያ አውጥቷል።

19.7 ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት ፕሮግራም ከኢትዮጵያ፣ ኢራቅ፣ አልቤኒያ፣ ባንግላዴሽ፣ ጋና፣ ሕንድ፣ ጀማይካ፣ ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን፣ ቬትናም እና ዚምባብዌ የመጡ ፍልሰተኞችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ያቀደ ነው።

ኮንትራክተሮቹ የምግብ አቅርቦት በማዳረስና የቤተሰብ ዓባላትን በማፈላለግ እንዲሁም ለፍልሰተኞቹ ሥራ በማፈለግ እንደሚረዱ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ማስታወቂያ ላይ ተመልክቷል።

ከዚህ ቀደም የእንግሊዝ መንግስት ከእ.አ.አ ጥር ወር 2022 በኋላ በፈረንሣይ አድርገው ወደ ሃገሪቱ የገቡ ፍልሰተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመውሰድ ያወጣው ዕቅድ በፓርላማው ቢፀድቅም፣ በፍ/ቤት የሕግ ሙግት ስለገጠመው እስከ አሁን ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።

የያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት 14ሺሕ ፍልሰተኞችን ለማስወጣት መታቀዱ ታውቋል።

በያዝነው ዓመት ብቻ ከ20ሺሕ በላይ ፍልሰተኖች በጀልባ ተጉዘው ከፈረንሣይ እንግሊዝ ገብተዋል።