የእንግሊዝ መንግስት በያዝነው የአውሮፓውኑ 2024 ቁጥራቸው 6,000 የሚሆን ስደተኞችን ‘ወደ ሩዋንዳ ያሸጋግራል’ ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ።
SEE ALSO: የእንግሊዝ ፓርላማ የሩዋንዳ ጥገኝነት ሕግ አፀደቀእንግሊዝ ወደ ሩዋንዳ የምትልካቸውን ስደተኞች የሚመለከተው ይህ አሃዝ ይፋ የተደረገው ሰሜናዊ አውሮፓን በአነስተኛ ጀልባዎች አቋርጠው የሚመጡትን ስደተኞች ሙከራ ለማስቆም የተያዘው ውጥን ለወራት ከዘለቀ የፓርላማ ውዝግብ በኋላ ጽድቆ የሃገሪቱ ሕግ በሆነ ቀናት ዕድሜ ውስጥ ነው።
SEE ALSO: በፍልሰተኞች ላይ የደረሰ አሰቃቂ አደጋ ብሪታኒያ ያፀደቀችው የሩዋንዳ ሕግ ትኩረት እንዲስብ አድርጓልየፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ሩዋንዳ በአሁኑ ወቅት እንግሊዝ ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 5,700 የሚደርሱ ስደተኞችን ለመቀበል “በመርህ ደረጃ” ተስማምታለች ሲል የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ከእነኚም መካከል 2,143 የሚሆኑት ወደሩዋንዳ ከመላካቸው አስቀድሞ "እስር ላይ ሊቆዩ መቻላቸውን" የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ አክሎ አመልክቷል።
የእንግሊዝ የጤና ሚንስትር ቪክቶሪያ አትኪንስ በበኩላቸው የሕግ አስፈጻሚ አካላት ቀሪውን ካሉበት ፈልገው ያመጣሉ ብለዋል አያይዘውም ማንኛውም ስደተኛ በደንቡ መሰረት መጥቶ ካልተመዘገበ ካለበት ተይዞ ይቀርባል’ ብለዋል።
ባለስልጣናቱ የመንግስት አኃዛዊ መረጃዎችን ጠቅሰው እንዳመለከቱት ባለፉት 18 ወራት ጊዜ ውስጥ በትናንሽ ጀልባዎች ተሳፍረው የእንግሊዝ ቻናልን ለማቋረጥ የሞከሩ ቁጥራቸው ከ57, 000 በላይ ፍልሰተኞች ከዚያች አገር ዘልቀዋል።