አንድነት ያዘጋጀው ውይይት ተካሄደ፡፡
አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ያዘጋጀውና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተካሄደ በኢትዮጵያ የጥበብ ሚና ወይም ሥፍራ ላይ የተነጋገረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
ገጣሚና ፀሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላት፣ ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ፣ ቀራጭና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በቀለ መኮንን ከአወያዮቹ መካከል ነበሩ፡፡
ግንቦት 12 ቀን 2004 ዓ.ም በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ መሪነቱን የያዙት ዕውቅ የኪነጥበብ ሰዎች ይሁኑ እንጂ ተሰብሣቢውም ሞቅ ባለ ስሜትና ፍላጎት ተሣትፏል፡፡
የውይይቱ ርዕስ የኪነጥበብ ሚና በሕብረተሰብ ውስጥ ምንድነው? የሚል ነበር፡፡
ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡