በደቡባዊ አፍሪካ 60 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ችግር እንዳለባቸው ተመድ አመለከተ

ፎቶ ፋይል፦ በኤልኒኖ ምክንያት በተፈጠረ ድርቅ ከጆሃንስበርግ ወጣ ብሎ በቫንደርቢጅል ፓርክ አቅራቢያ ያለ የበቆሎ እርሻ እአአ ጥቅምት 1/2015

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ 60 ሚሊዮን የሚደርሱ የደቡባዊ አፍሪካ ሕዝቦች፣ በኤልኒኖ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ለምግብ ዋስትና ዕጦት መዳረጋቸውን አመልክቷል፡፡

ችግሩ ያለው በማላዊ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ብቻ ሳይኾን፣ ዓለም አቀፍ የርዳታ ጥሪዎችን ባቀረቡ ሀገራትም እንደኾነ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡባዊ አፍሪካ 60 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ችግር እንዳለባቸው ተመድ አመለከተ

ኮሎምበስ ማቭሁንጋ ከዚምባብዌ እንደዘገበው፣ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት፣ ቀውሱን ለማቃለል ተስፋ በማድረግ 10 ሚሊዮን ዶላር እየለቀቀ ነው።