የሚነሶታ ፖሊስ፡ ሁለት ኢትዮጲያውያን ሞቱ ፣ አንዱ ደግሞ የከፋ ጉዳት ደርሶበታል

ፖሊስ

ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑ ታውቋል።

ባለፈው እሁድ እአአ ሕዳር 22 2015 ምሽት ላይ ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን የሚንያፖሊስ ከተማ ፖሊስ ጆን አልደር (John Elder) ለCBS ቴለቪዥን ገልጿል።

"የከተማው ፖሊሶች በወቅቱ ቦታው ላይ የነበሩ ሰዎችን እያነጋገሩና ጉዳዮን እየመረመሩ ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎቹ ወድያው በእግር እንደሸሹና እስካሁንም እንዳይልተያዙ" ጆን አልደር ገልጸዋል። የቪድዮ ቃለ ምልልሱን ከዚህ ፋይል ይመልከቱ።

የሚንያፖሊስ ከተማ ፖሊስ ባጅ

ፖሊስ የነዚህን ወጣቶች ማንነት ይፋ ያላደርገ ሲሆን የከተማይቱ ነዋሪዎች ሦስቱን ወጣቶች ኦሮሞ መሆናቸውን ይናገራሉ። በትናንትናው ዕለት ፖሊስ መግለጫ ሲሰጥ፣ በስፍራው የተገኙና የብራየን ኮይል ኮሚዩኒቲ ዳይረክተር (Brian Coyle Community Director) የሆኑት አቶ አማኖ ዱቤ "እነዚህ ልጆች ሦስቱም ኦሮሞች ናቸው የኮሌጅ ተማሪዎችም ነበሩ። የሚንያፖሊስ ፖሊስ፣ ወጣቶቹ ሙስሊም ስለሆኑና በቶሎ መቀበር እንዳለባቸው ስለምናውቅ፣ ምርመራውን በቶሎ ለመጨረስ እንሞክራለን ብለውናል" ብለዋል።

ዝርዝሩን ለመስማት ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በሚነሶታ ሁለት ኢትዮጲያውያን ሞቱ ፣ አንዱ ደግሞ የከፋ ጉዳት ደርሶበታል