የ2020 የህክምና የኖቤል ተሸላሚዎች

  • ቪኦኤ ዜና

የዘንድሮ የ2020 የህክምና የኖቤል ሽልማት ሃርቬይ ጄ አልተር፣ ሚካኤል ሃውተን እና ቻርለስ ኤም ራይስ ለተባሉ የሳይንስ ጠቢባን ተሰጥቷል።

ሦስቱ የሳይንስ ምሁራን የኖቤል ሽልማቱን ያገኙት ሂፐታይተስ ሲ ቫይረስን በሚመለከት ላደረጓቸው ጥናቶችና ለግኝቶቻቸው መሆኑን ተገለጿል።

የሳይንስ ጠቢባኑ ጥናቶችና ግኝቶች የሂፐታይተስ ሲ በሽታን ለማከምና ለማዳን አዲስ መንገድ ወደ ማግኘት ለማምራት ይረዳሉ ተብሏል።

የኖቤል ተሸላሚዎቹ እያንዳንዳቸው $1.1 ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ።

የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪ፣ የሥነ ጽሁፍና የሰላምኖቤል ሽልማቶች ደግሞ እስከ መጭው አርብ ባለው ጊዜ በየቀኑ ይፋ እንደሚደረጉ የኢኮኖሚ ሳይንስ ሽልማት ደግሞ በመጭው ሰኞ እንደሚገለጽ ታውቋል።