በእስራኤል ወታደሮች የምዕራብ ጋዛ አሰሳ ሁለት ፍልስጤማውያን ቆሰሉ

የጄኒን ገዥ አክራም ራጁብ

የጄኒን ገዥ አክራም ራጁብ

በኃይል በተያዘችው ምዕራብ ጋዛ ዳርቻ፣ በሙስሊም የቅዱስ ሮሞዳን ጻም ወር ውስጥ፣ በመካሄድ ላይ በሚገኝ ጥቃት፣ ሁለት ፍልስጤማውያን በእስራኤል ኃይሎች በጽኑ መቁሰላቸውን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የእስራኤል ወታደራዊ ክፍል ዛሬ ሰኞ በሰጠው መግለጫ፣ ወታደሮቹ በሰሜን ጋዛ በምትገኘው ጄኒን ምዕራባዊ ክፍል በያሙን መንደር፣ ተፈላጊዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል እርምጃ መውሰዳቸውን ገልጿል፡፡

በርካታ ፍልስጤማውያን ድንጋይና ተቀጣጣይ ነገሮችን ወደ ወታደሮቹ የወረወሩ ሲሆን፣ ወታደሮቹም በአጸፋው የተኩስ ምላሽ መስጠታቸው ተመልክቷል፡፡

በጽኑ ቆስለዋል የተባሉት ሁለቱ ፍልስጤማውያን ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተዘግቧል፡፡

በቅርብ ሳምንታት በተካሄደ ጥቃት ሰዎች የተገለዱባት እስራኤል ጥቃቱን ያደረሱትን ሰዎች ለመያዝ በርካታ የፍስልጤማውያን ከተሞችን የሚያስሱ ወታደሮችን ማሰማራቷ ተነገሯል፡፡

ባለፈው ወር በቴላቪቭ በሚገኝ አንድ መጠጥ ቤት አንድ ፍልስጤማዊ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ ሦስት ሰዎች በመግደል አካባቢውን ለቆ የተሰወረ ሲሆን፣ ቆየት ብሎ በተካሄደ አሰሳ፣ ከፖሊስ ጋር በተካሄደ ግጭት መገደሉ ተገልጿል፡፡

በእስራኤል ለዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በተፈጸሙ ሌሎች ሦስት ጥቃቶች፣ 14 ሰዎች መገደላቸው በአሶሼይትድ ፕሬስ ዘገባ ተመልክቷል፡፡