የቱርክ ፓርላማ ዓባላት ድብድብ

  • ቪኦኤ ዜና
በቱርክ ፀረ መንግስት የተቃውሞ ሰልፍ አስተባብረዋል በሚል የታሰሩ፣ በኋላ ግን በፓርላማ አባልነት የተመረጡ ተቃዋሚ ፖለቲካኛ በፓርላማው እንዲሳተፉ ሊፈቀድላቸው ይገባል ሲሉ አንድ ተቃዋሚ ዓባል ጥያቄ በማቅረባቸው ከገዢው ፓርቲ ዓባላት ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።

የገዢው ኤኬፒ ፓርቲ ዓባላት ተቃዋሚው አህመት ሲክ ንግግር ወደሚያደርጉበት አትሮንስ በመሄድ ድብደባ ሲፈጽሙባቸውና ሌሎች አባላት ደግሞ ለማስቆም ሲታገሉ ተስተውሏል። ወደ መድረኩ የሚወስደው ነጭ ደረጃም በደም ተለውሶ ተስተውሏል።

ፀረ መንግስት ሰልፍ አስተባብረሃል በሚል ወደ እስር ቤት የተወረወሩት ካን አታላይ የተባሉት ፖለቲከኛ ከሁለት ዓመታት በፊት ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋራ ለእስር ቢዳረጉም፣ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር በተደረገው ምርጫ የሠራተኛ ፓርቲውን በመወከል በፓርላማ ዓባልነት ተመርጠው ነበር። ፓርላማው ወንበራቸውን ቢቀማም፣ ሕገ መንግስታዊው ፍ/ቤት ውሳኔውን ውድቅ አድርጎት ነበር።

ካን አታላይ ወደ ፓርላማው መመለስ አለባቸው ሲሉ ለፓርላማው ንግግር ያደረጉት አህመት ሲክ “ካን አታላይን ሽብርተኛ ብላችሁ መጥራታችሁ አይገርመኝም፣ ከእናንተ ያልወገነውን ሁሉ በሽብርተኛነት ስለምትፈርጁ፤ ትልቁ ሽብርተኞች ግን እናንተ ናችሁ” ማለታቸውን ተከትሎ፣ ድብድቡ መጀመሩ ታውቋል።