አንድ ታጣቂ፣ በኢራቋ የኩርዶች ከተማ አረቢል ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ በዛሬው ቀን በፈፀመው ጥቃት፣ እስካሁን በተረረጋገጠው መሠረት አንድ የቱርክ ዲፕሎማት መገደሉን፣ መንግሥዊው የቱርኩ ዜና አውታር ዘግቧል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
መንግሥታዊው ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ የቱርክ ምክትል ዋና ቆንስላ የነበረው ዲፕሎማት አረቢል ውስጥ በሚገኘው የቆንስላ ጽ/ቤት በሥራ ገበታው ላይ ነበር።
ሌሎች በርካታ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው የተዘገበ ቢሆንም፣ እስካሁን ግን የሞቱትንም ሆነ የቆሰሉትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ማወቅ አልተቻለም።