ቱርክ በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ሸቀጣ ሸቀጥ ላይ የቀረጥ ክፍያውን ከፍ እንደምታደርግ ዛሬ አስታውቃለች።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ቱርክ በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ሸቀጣ ሸቀጥ ላይ የቀረጥ ክፍያውን ከፍ እንደምታደርግ ዛሬ አስታውቃለች።
በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለው ግንኙነት እየሻካረ በሄደበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ሀገሮች ሲነታረኩ ቆይተዋል። ቱርክ ከዩናይትድ ስቴትስ በምታስገባቸው ተሽከርካሪዎች፣ የአልኮል መጠጥ፣ ከሰል፣ ሩዝና መዋብያ ሸቀጦች ላይ ነው ቀረጥ የምትጨምረው።
የቱርክ ምክትል ፕሬዚዳንት ፋቱ ኦታየ ሀገራቸው ቀረጥ የመጨመር ዕርምጃ የወሰደችው ከዩናይትድ ስቴትስ ለሚደርስብን የኢኮኖሚ ጥቃት ምላሽ ነው ሲሉ በትዊተር ጽፋዋል።
የቱርክ ፕረዚዳንት ሬጂብ ታይፕ ኤርዶዋን የዩናይትድ ስቴትስ የኤለክትሮኒክ ዕቃዎች መግዛቱን ለማቆም ትላንት ዝተው ነበር። አሜሪካ በቱርክ ላይ ዒላማ የለየ የኢኮኖሚ ጦርነት እያካሄደች ነው በማለትም ከሰዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።