የፕሬዚዳንት ትረምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲ

  • ቪኦኤ ዜና
አጋር ሀገሮች የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲን የሚንቅፉ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ በመጪው የቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ በአቋማቸው እንደሚፀኑ ከዋና የኢኮኖሚ አማካሪዎቻቸው አንዱ ትላንት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

አጋር ሀገሮች የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲን የሚንቅፉ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ በመጪው የቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ በአቋማቸው እንደሚፀኑ ከዋና የኢኮኖሚ አማካሪዎቻቸው አንዱ ትላንት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

“ፕሬዚዳንቱ እነዚህ ከባድ ጉዳዮች አያስጨቋቸውም። ምን ጊዜም ቢሆን በዩናይትድ ስቴትስና በቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መካከል ስለሆነ ነገር ውጥረት አለና” ሲሉ የብሄራዊ ኢኮኖሚ ካውንስል ሥራ አስኪያጅ ላሪ ኩድሎው አስገንዝበዋል።

ኩድሎው በዋይት ኃውስ ቤተመንግሥት በተደረገው ጋዜጣዊ ጉባዔ ይህን ያሉት የቡድን ሰባት ጉባዔን የሚያስተናግዱት የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃስቲን ትሩዶና የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል ነገና ቅዳሜ በማካሄደው ጉባዔ ላይ ከባድ ውይይት እንደሚደረግ ከገለፁ በኋላ ነው።