ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በሰፊው እንደሚያሸንፉ የተተነበየላቸውን የዲሞክራቲክ ፓርቲውን ተቀናቃኛቸውን ሂላሪ ክሊንተንን በአስገራሚ ሁኔታ አሸንፈው 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ተመርጠዋል።
አዲስ አበባ —
ተዋናዩና ከበርቴ ነጋዴው ትራምፕ ለሊቱን በማንሃትን ሆቴል አዳራሽ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው የድል ንግግር ያሰሙት በከፍተኛ የደስታ ስሜት ነው።
የኒውዮርክ ነጋዴ በምርጫው ዘመቻው ወቅት በሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች ተቀድመው ነበር የታዩት ሆኖም በትናንቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማጠቃልያ ምሽት ግን በአስደናቂ ሁኔታ በድል አድራጊነት ብቅ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ሆነዋል፡፡
በዋይትሃውስ ቤተመንግሥት የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ሜሪ አልያስ ሳሊናስ በሥፍራው ነበረች፤ ያደረሰችንን ዘገባ ሰሎሞን ክፍሌ ያቀርበዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5