የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ "ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ፈጽሞ እንዳይዝቱ" ሲሉ የኢራኑን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒን አስጠነቀቁ።
ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ የኢራንን መሪዎች የሚነቅፍ ንግግር ካደረጉ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው።
ሚስተር ትረምፕ ለኢራኑ ፕሬዚዳንት ሩሃኒ ብለው ትናንት ዕሁድ ማታ በትዊተር ባወጡት ማስጠንቀቂያቸው እንዲህ ብለው
"ዩናይትድ ስቴትስ ላይ እንዳይዝቱ አለበለዚያ በታሪክ ታይቶ የማያውቅ መዘዝ ያገኝዎታል ። የሚሰነዝሩትን የዕብደት ዛቻ እንደድሮው ዝም ብለን የምንመለከት አይደለንም ተጠንቀቁ" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህን ማስጠንቀቂያ ያወጡት የኢራኑ ፕሬዚዳንት "በአንበሳ ጭራ መጫወት ይቅርቦት በኋላ ይቆጭዎታል" ብለው ትረምፕን አስጠነቀቁ የሚሉ ሪፖርቶች ቀደም ብለው ከተሰሙ በኋላ ነው።
ሩሃኒ "ከኢራን ጋር ሰላም መፍጠር የሰላም ሁሉ መጨረሻ ከኢራን ጋር ጦርነት ማንሳት ጦርነትም የጦርነት ሁሉ መጨረሻ አሜሪካ ቢገባት ይሻላ" ማለታቸው ተጠቅሷል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖምፔዎ ካልፎርኒያ ውስጥ ባደረጉት ንግግር የኢራን መንግሥት ለሀገሩ ህዝብ ከባድ ስቃይ ሆኖበታል ብለዋል።