ትረምፕ በአዲሱ ቀረጥ ጉዳይ የካናዳውን ትሩዶን አነጋገሩ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል - ዩናይትድ ስቴትስን፣ ካናዳ እና ሜክሲኮን የሚወክሉ ብሔራዊ ባንዲራዎች በኒው ኦርሊየንስ እአአ ሚያዝያ 21/2008

ፎቶ ፋይል - ዩናይትድ ስቴትስን፣ ካናዳ እና ሜክሲኮን የሚወክሉ ብሔራዊ ባንዲራዎች በኒው ኦርሊየንስ እአአ ሚያዝያ 21/2008

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ የጣሉት አዲስ ቀረጥ ተፈጻሚ ከመደረጉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር ዛሬ መነጋገራቸውን አስታወቁ።

‘ትሩዝ ሶሻል’ በተባለው የራሳቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አውታር ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ከሰአት በኋላ ላይ ትሩዶን እንደገና አነጋግራቸዋለሁ ያሉት ትረምፕ፤ አዲሱ ቀረጥ ካናዳ ወደ አሜሪካ የሚገባውን ለብዙ ህይወት መጥፋት ምክኒያት የሆነ ‘ፌንቲኔል’ የተባለ አደገኛ መድሃኒት ቁጥጥር እንድታጠነክር ለማስገደድ ነው ሲሉ ይሞግታሉ።