የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ የግድያ ሙከራ በተደረገባቸው በሁለተኛው ቀን ዛሬ፣ሰኞ በሚጀመረው የፓርቲያቸው ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ። ከዛሬ ሰኞ እስከ ሐሙስ የሚካሄደውን እና እርሳቸውን በይፋ ፕሬዝደንታዊ እጩ አድርጎ የሚመርጠውን ጉባኤ ሙሉውን አራቱንም ቀናት እንደሚሳተፉም ታውቋል። ትረምፕ የግድያ ሙከራ በተደረገባቸው ማግስት፣ ትላንት እሁድ ጉባኤው በሚካሄድባት መልዎኪ ገብተዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
የትረምፕን የግድያ ሙከራ ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው ይበልጥ ተነቃንቀዋል
የቪኦኤ የዋሽንግተን ከፍተኛ ዘጋቢ ካሮሊን ፐርሱቲ በመልዎኪ፣ ውስካንስን በመገኘት የግድያ ሙከራውን ድንጋጤ ተከትሎ የትረምፕ ደጋፊዎች እንዴት እንደተነሳሱ ተመልክታለች፡፡
እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።