በትራምፕ ላይ የደረሰውን የግድያ ሙልከራ ተከትሎ ባይደን ሃዘኔታ በተመላው የዋይት ሃውስ ንግግራቸው የአንድነት እና የሰላም ጥሪ አቀረቡ

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትላንትናው ከአንድ ቀን በፊት በተቀናቃኝ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተቃጣውን አስደንጋጭ የግድያ ሙከራ ተከትሎ አሜሪካውያን አንድ እንዲሆኑ እና ከፖለቲካ ሁከት እንዲርቁ ለመማፀን የጽ/ቤታቸውን ሙሉ ኃይል ተጠቅመዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በትራምፕ ላይ የደረሰውን የግድያ ሙልከራ ተከትሎ ባይደን ሃዘኔታ በተመላው የዋይት ሃውስ ንግግራቸው የአንድነት እና የሰላም ጥሪ አቀረቡ

የፓርቲያቸው ፕሬዚዳንታዊ እጩ ሆነው ወደሚመረጡበት እና በዛሬው ዕለት ወደተጀመረው የሪፐብሊካን ፓርቲ ጉባኤ ያቀኑት ትራምፕም ተመሳሳይ ጥሪ አሰምተዋል። የሁለቱም በጥቅምት ወር መገባደጂያ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ከምርጫው አስቀድሞ ሊደርስ የሚችል አደጋ እንዳሳሰባቸው የሚያመላክት እርምጃ መሆኑን ተቅሳ የአሜሪካ ድምጽ የዋይት ሃውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ያደረሰችንንን ዘገባ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።