Your browser doesn’t support HTML5
ትረምፕ ሩሲያ የዩክሬይኑን ጦርነት እንድታቆም ብርቱ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው
ከጥቂት ቀናት በፊት አስተዳደሩን ተረክበው ሥራቸውን የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሩሲያ ከዩክሬይን ጋራ የሰላም ንግግር እንድትጀምር ግፊታቸውን በማጠናከር ላይ ናቸው። "የሰላም ንግግር አላደርግም ብትል ዩናይትድ ስቴትስ አዳዲስ ማዕቀቦች እና ታሪፎች ትጥልባታለች" በማለት ትረምፕ ያሰሙትን ዛቻ ሩሲያ አጣጥላዋለች።
የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሊሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።