ትረምፕ የፖላንዱን ፕሬዚደንት እራት ጋበዙ

ፎቶ ፋይል፡- የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ከፖላንዱ ፕሬዝደንት አንድሬ ዱዳ ጋር

ፎቶ ፋይል፡- የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ከፖላንዱ ፕሬዝደንት አንድሬ ዱዳ ጋር

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ከፖላንዱ ፕሬዝደንት አንድሬ ዱዳ ጋራ ትናንት ረቡዕ በኒው ዮርክ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ትረምፕ በድጋሚ ሊመረጡ ይችላሉ በሚል አውሮፓ በዝግጅት ላይ ስትሆን፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንትም የውጪ ሃገራት መሪዎችን ማነጋገራቸውን ቀጥለዋል።

ትረምፕ ለፖላንዱ መሪ ኒው ዮርክ በሚገኘው ሕንጻቸው የእራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።

የዩክሬን ጠንካራ ደጋፊ የሆኑት አንድሬ ዱዳ፣ ዋሽንግተን ለኪቭ ተጨማሪ ርዳታ እንድታደርግ ያበረታታሉ።

“አኩሪ ሥራ ሠርተዋል። ወዳጄም ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል ትረምፕ፡፡ “ግሩም አራት ዓመታትን አሳልፈናል። ሁሌም ፖላንድን እንደግፋለን” ሲሉም አክለዋል።

በእ.አ.አ 2016 በነበረው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ትረምፕ አሸናፊ ሆነው ሲወጡ፣ የአውሮፓ ሃገራት ክስተቱ ድንገተኛ ስለሆነባቸው ከሁኔታዎች ጋራ ራሳቸውን ለማስተካከል ሲራኩቱ ነበር ሲል አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው አመልክቷል። የአውሮፓ መንግሥታት ያ ሁኔታ እንዲደገም እንደማይሹና ዝግጁ ሆነው መጠበቅን እንደመረጡም ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።