ትረምፕ ክስ ቀረበባቸው

  • ቪኦኤ ዜና

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ "ዋይት ሃውስን ለቀው ሲወጡ፣ ሚስጥራዊ የመንግሥት ሰነዶችንም ይዘው ወጥተዋል" ሲል ፍሎሪዳ የሚገኝ የፌዴራል ፍርድ ቤት ክሥ አቅርቦባቸዋል።

⁣የአገሪቱ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ክሱን ለትረምፕ ጠበቆች ያስታወቀ ሲሆን፣ ትረምፕም መከሰሳቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ መድረካቸው አረጋግጠዋል።⁣

⁣“በሚያሳዝን ሁኔታ አገሪቱ ቁልቁል እየሄደች ነው። በታሪክ ከየትኛውም ተመራጭ ፕሬዚደንት ከፍተኛ ድምጽ ያገኘ ሕዝባዊ ፕሬዚደንት ላይ ክስ አቅርበዋል። እኔ ንጹሁ ሰው ነኝ” ብለዋል ትረምፕ፡፡⁣

⁣የትረምፕ ጠበቃ ጄምስ ትረስቲ ለሲኤን ኤን እንደተናገሩት ፣ ሆን ብሎ የብሔራዊ ጸጥታ መረጃዎችን መያዝ፣ የሐሰት ቃል መስጠት እና በመንግሥት ላይ ማሴር የሚሉት ከክሶቹ ውስጥ ይገኙበታል።⁣

⁣የቀድሞው ፕሬዚደንት በፍሎሪዳ በሚገኘው ፍ/ቤት ማክሰኞ እንደሚቀርቡ እና የክሶቹም ብዛት ሰባት እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኞች ለአሶሽየትድ ፕሬስ ተናግረዋል።⁣

⁣ክሡ ትረምፕን በአሜሪካ ታሪክ ከሥልጣን ዘመን በኋላ የተከሰሰ የመጀመሪያው የቀድሞ ፕሬዚደንት ያደርጋቸዋል።⁣ የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ ሰዎች ባለፈው ነሐሴ ማር አ ላጎ የሚገኘውን የትረምፕ ቤት ሲፈትሹ፣ ከ100 በላይ ሚስጥራዊ ሰነዶችን አግኝተዋል።⁣ ከሰነዶቹ ጋር በተያያዘ ምንም ጥፋት እንደሌለባቸው ትረምፕ ይናገራሉ።⁣