ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለ ሰሜን ኮርያ

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ በምትደቅነው የኑክሌር መሣርያ አደጋ ምክንያት አዲስ ማዕቀቦችን እንደሚጥሉ ገልፀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ በምትደቅነው የኑክሌር መሣርያ አደጋ ምክንያት አዲስ ማዕቀቦችን እንደሚጥሉ ገልፀዋል።

በሰሜን ኮርያ ላይ ስላላቸው ፍጥጫ ስትራቴጂ ለማውጣት ሲሉ ከደቡብ ኮርያና ከጃፓን መሪዎች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር እየተዘጋጁ ነው።

ትራምፕ በዛሬ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ከደቡብ ኮርያው ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ኢን ጋርና ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር ምሳ ላይ በተናጠል ከተነጋገሩ በኋላ አንድ ላይ ተሰባስበው ይነጋገራሉ።

ሰሜን ኮርያ በተደጋጋሚ ስለምታካሄደው የኑክሌርና በቦሊስቲክ ሚሳይል ፍተሻዎች እንደሚነጋግሩ ታውቋል።

ትራምፕ በሰሜን ኮርያ ላይ አዲስ ማዕቀቦች እንደሚጥሉ አስታውቀዋል። ሆኖሞ የተባበሩት መንግሥታ ትድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ከጣልቸው የሰሜን ኮርያን ወደ ውጭ የሚላኩ ዕቃዎችንና የኃይል አቅርቦትዋን ኢላማ ከሚያደርጉ ማዕቀቦች በምን እንደሚለይ እስካሁን ባለው ጊዜ ግልፅ አይደለም።