የዩናይትድ ስቴትስ የክፍላተ ሀገር አገረ ገዢዎች ዛሬ ሰኞ ዋሺንግተን ውስጥ በሚያካሂዱት ጉባዔ በቅርቡ ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት የደረሰው ጥቃት ዋናው ትኩረት እንደሚሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ የክፍላተ ሀገር አገረ ገዢዎች ዛሬ ሰኞ ዋሺንግተን ውስጥ በሚያካሂዱት ጉባዔ በቅርቡ ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት የድረሰው ጥቃት ዋናው ትኩረት እንደሚሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ።
ፕሬዚዳንቱ ትናንት ዕሁድ ማታ ጉባዔተኞቹን ለመቀበል በተካሄደ ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር እንደሚመስለኝ ዋናው አጀንዳችን ይሆናል። ምክንያቱም ይሄን ሃገራችን ውስጥ እየሆነ ያለውን ነገር ማክተም ስላለብን ብለዋል።
የተለያዩ የአሜሪካ ክፍላተ ሀገር የተለያዩ የመሳሪያ ሕግጋት ያሏቸው በመሆኑ አዲስ የመሳሪያ ቁጥጥር ደንቦችን መደንገግ ማስፈለጉ ላይም ሆነ እንዴት እንደሚደነገግ የተለያዩ ሃሳቦች ሊሰነዘሩ ይችላሉ። ፌዴራሉ መንግሥት ደግሞ የራሱን ዕርምጃ ሊወስድ ይችላል።
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላትም አንድ ሳምንት በየክፍለ ሃገራቸው ክርመው ዛሬ ወደ ምክር ቤቱ ተመልሰዋል።
ወደፊት በትምህርት ቤቶች የተኩስ ጥቃት እንዳይደርስ ለመከላከል መወሰድ በሚገባቸው ዕርምጃዎች ዙሪያ ክርክሩ ተጧጡፎ ቀጥሏል።
ይህ የቅርብ ጊዜው ግድያ ምክር ቤቱን አንዳች ዕርምጃ እንዲወስድ ያንቀሳቅሰው እንደሆን ግን አይታወቅም፡፡