የታላቁ ኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ዋሺንገተን ዲሲ እያካሄዱት ያለው ንግግር አራተኛ ቀኑን ይዟል። ተጨባጭ ሥምምነት ላይ ለመድረስ እየታገሉ ነው ተብሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ እንደተነጋገሩ የዋይት ኃዋስ ቤተመንግሥት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። “በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ ወደ መድረስ ተቃርቧል” በማለት ብሩህ ተስፋ ማንጸባረቃቸውንና የሚመለከታቸውን ሁሉ ይጠቅማል” ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።