Your browser doesn’t support HTML5
ትራምፕ በዓለም ጤና ድርጅት እና የአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያሳለፏቸው ትዕዛዞች በአፍሪካ እና ቻይና ላይ ተጽእኖ አላቸው
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ቀን፣ አሜሪካን ከፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት እና ከዓለም ጤና ድርጅት የማውጣት ሂደት የሚያስጀምሩት የማስፈፀሚያ ትዕዛዞች ፈርመዋል። አንድ የአፍሪካ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን በውሳኔው ላይ ተጨማሪ መረጃ እንደሚጠብቁ ሲናገሩ፣ ተንታኞች ግን የትራምፕ ውሳኔ ለቻይና ተጨማሪ በር የሚከፍት ነው ብለዋል። ኬት ባርትሌት ከጆሃንስበርግ ያደረሰችንን ዘገባ፣ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።