ፕሬዚደንት ትረምፕ ከክሪስትያን ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ቃለ ምልልስ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ክሪስትያን ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ከሚባል የሥርጭት መረብ ጋር ትናንት - ረቡዕ ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ከሩስያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳላደረጉ ገልፀዋል።

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ክሪስትያን ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ከሚባል የሥርጭት መረብ ጋር ትናንት - ረቡዕ ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ከሩስያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳላደረጉ ገልፀዋል።

ልጃቸው ዶናልድም እንዲሁ የዩናይትድ ስቴትስን ምርጫ በሚመለከት ከሩሲያ ባለሥልጣናት ጋር አልተገናኘንም ሲሉ አስተባብለዋል።

ይሁንና የሚስተር ትረምፕ የምርጫ ዘመቻ ባለሥልጣትና አንድ የሩሲያ የህግ ባለሙያ መገናኘታቸውን፤ የትረምፕ ተፎካካሪ የነበሩትን ዴሞክራቷን ሂለሪ ክሊንተንን ከጨዋታ ውጪ ሊያደርግ የሚችል መረጃም እንዳቀበሏቸው በሰፊው መናፈሱ ይታወቃል።

የቪኦኤው ጂም መሎን ከዋሺንግተን ተጨማሪ ዘገባ ልኳል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ፕሬዚደንት ትረምፕ ከክሪስትያን ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ቃለ ምልልስ