ትረምፕ - በአሪዞና

  • ቪኦኤ ዜና
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት በአሪዞና ክፍለ ግዛት ጉብኝት አደረጉ። ፕሬዚዳንቱ በአሁኑ ጊዜ ለጤና ሠራተኞች የሚውሉ የአፍና የአፍንጫ መሸፈና ጭምብሎች፣ ማምረት ላይ የተሰማራ የኤሮስፔስ ቁሳቁስ አምራች ኩባንያ ጉብኝተዋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት በዩናይትድ ስቴትስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ያሻቅባል፣ የሚለውን አዲስ ትንበያ አስተዳደራቸው እያጣጣለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ነው - ፕሬዚዳንቱ የአስተዳደራቸውን ጥረት አጉልተው ለማሳየት በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ቁልፍ ቦታ ወደ አላት አሪዞና የተጉዞት፤ መሰል ጉብኝቶችም ታቅደዋል።