ሄይቲ ከባድ እና ሃይለኛ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ አስግቷል

  • ቪኦኤ ዜና

በሄይቲ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ፤ ህክምና ሲደረግላቸው

ባለፈው ቅዳሜ በሰው ህይወት እና ንብረት መጠነ ሰፊ ጉዳት ባደረሰ ከባድ የመሬት ነውጥ በተመታችው በሄይቲ፤ ከባድ ንፋስ የቀላቀለ ሃይለኛ ዝናብ እየጣለ ነው።

እስከ አስራ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ዝናብ እንደሚጥል የአየር ሁናቴ ትንበያ አዋቂዎች ሰግተዋል። በዚህም የተነሳ የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል።

ከመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በህይወት የተረፉ ሰለባዎችን ለመፈለግ እና ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ እርዳታ ለማድረስ የተያዘውን ጥረት ዝናቡና ንፋሱ ሊያስተጓጉል እንደሚችል ባለሥልጣናቱ ፈርተዋል

ትናንት የሄዪቲ ባለሥልጣናት እንዳሉት በመሬት ነውጡ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1420 ደርሷል፤ ቢያንስ 6000 ሰዎች በአደጋው ቆስለው ህክምና ላይ ናቸው።