ጉባኤ ያካሄደው ህወሓት አቶ ጌታቸውን ጨምሮ 16 አመራሮችን ከፓርቲው ማባረሩን ገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

ጉባኤ ያካሄደው ህወሓት አቶ ጌታቸውን ጨምሮ 16 አመራሮችን ከፓርቲው ማባረሩን ገለፀ

በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ የተመረጠው አዲሱ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 16 አመራሮቹን ከፓርቲው ማባረሩን እና ፖለቲካዊ ስራዎች እንዳይከውኑ ማገዱን አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያላቸው ኃላፊነት ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ እንደሚፈልግ ገልጿል።

ታግደዋል ከተባሉ አንዱ እና የክልሉ የኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም: በህገወጥ ጉባኤ የተመረጠ ቡድን የሚወስነው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም በማለት አጣጥለዉታል፡፡

ሰላም የማይቀበል ቡድን ነው ያሉት አቶ ረዳኢ ክልሉን ላይ ተጨማሪ አለመረጋጋት ለመፈጠር ያቀዱ ናቸው ሲሉ ከሰዋል፡፡